በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጭው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሰው


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛው የሥልጣን ዘመቻቸው እየተዘጋጁ በነበሩበት ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሂላሪ ክሊንተን ኃላፊነታቸውን እንደሚለቅቁ ተናግረው ነበር፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:07:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለመሥሪያ ቤታቸው ሠራተኞች ሲናገሩ ማረፍ እንደሚፈልጉ ጠቁመው ነበር፡፡

“በርግጥ - አሉ ክሊንተን - ፕሬዝዳንቱ አንድ ሰው መርጠው ሽግግሩ እስኪጠናቀቅ እቆያለሁ፡፡ ሆኖም ግን ላለፉት ሃያ ዓመታት እጅግ በጋለው የአሜሪካ ፖለቲካና በሚያጅቡትም ፈተናዎች ውስጥ ከቆየሁ በኋላ ምን ያህል እንደደከመኝ መገንዘብ ምናልባት ጥሩ ሃሳብ ይመስለኛል፡፡”

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቃባይ ቪክቶሪያ ኑላንድ እንደሚሉት ከፕሬዝዳንቱ በድጋሚ መመረጥ በኋላም ያ ጉዳይ በዕቅድ ያለ ነው፡፡

“እርሣቸውን የሚተካቸውን ሰው አረካክበው እስኪጨርሱ እንደሚቆዩ እና ከዚያም ሃሣባቸውን ወደሚያሰባስቡበት እና ወደሚፅፉበት፣ እንዲሁም ሌላም የግል ህይወታቸው የመግባት ዕቅድ እንዳላቸው ደጋግመው ተናግረዋል፡፡” ብለዋል ኑላንድ፡፡

እና ሚስ ክሊንተንን እንዲተካላቸው ፕሬዝዳንት ኦባማ የሚመርጡት ተከታይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማን ይሆን?

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG