በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


Los Angels Times የተባለው ጋዜጣ ድረ-ገጽ በአሁኑ ወቅት በእስር የምትገኘው የ 31 አመት እድሜ ርእዮት አለሙ ባለፈው ሳምንት በጋዜጠኝነት ስራቸው ባሳዩት ብርታት ከተሸለሙት ሴት ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ሆናለች ይላል።

ርእዮት ተሸላሚ የሆነችው ባለፈው ሰኞ በበቨርሊ ሂልስ ሆቴል በተደረገው አለም አቀፍ የሴቶች ሚድያ ተቋም ባዘጋጀው አመታዊ የሽልማት ስነስርአት እንደሆነ ጋዜጣው ጠቅሷል። ተቋሙ በሙያቸው ብርታት ያሳዩ ሴት ጋዜጠኞችን በመሸለም የክብር ቦታ ይስጣል ሲል ጋዜጣው ጠቅሷል።

IRIN የተባለው የሰብአዊ ዜናና ትንተና አገልግሎት ደግሞ ኢትዮጵያ በውጭ በሚደገፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ቡድኖች ላይ የምታደርገው ገደብ እየጨመረ በሄደበት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን የቡና ምርት ከፍ ያደረጉት የአገር ውስጥ የህብረት ስራዎች የኢኮኖሚ ልማት ተምሳሌት ተደርገው እየተወሰዱ እንደሆነ
ጠቁሟል።

እነዚንና ሌላ ርእስንም ያቀፈው ዝግጅታችንን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።

AMH-Ethiopia-Press-Review-11-9-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG