ሃያ አራት ሰዓታት የማይሞላ ጊዜ የቀረው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምን ይሆን ውጤቱ? ብዙዎች በጉጉት የሚያነሱት የሰዓቱ ጥያቄ ነው።
ለመሆኑ፥ ዋና ዋና በሚባሉት መራጩ ሕዝብ በሚያነሳቸው ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የትኛው እጩ፥ ምን ዓይነት አቋም አላቸው?
የምርጫው አሸናፊ ማንነት፤ በመጪው አራት ዓመታት የአገሪቱን ገጽታ ብቻ ሳይሆን፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያስከትል ከሚችላቸው ተጽእኖዎች አንጻር፥ ይበልጥ አጓጊ ገጽታ በተላበሰው የነገው ምርጫ፤ የሁለቱን እጩዎች ማንነት፥ ይልቁንም የሚያራምዷቸውን ፖሊሲዎች ምንነት የሚዳስስ ትንታኔ ነው።
እጩዎቹ የመራጩን ቀልብ ለመሳብ በዘመቻዎቻቸው ከሚናገሩት ባሻገር፥ በታወቁ ቁልፍ-ቁልፍ ጭብጦች ዙሪያ በተጨባጭ ምን ዓይነት ፖሊሲዎችን ነው እያራመዱ ያሉት?
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም፥ በሳንበርናንዲኖው የካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የሕግ ባለ ሞያ ናቸው። ይተነትኑልናል።