በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ “ወደር የሌለው” ጥረት


ሶማሊያ
ሶማሊያ

አዲሱ የሶማሊያ መንግሥት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሃገሪቱን መልሶ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት “ወደር የሌለው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ዌንዲ ሸርማን አሞገሱ፡፡


ሚስ ሸርማን ይህንን የተናገሩት ሞቃዲሾ ውስጥ ያደረጉትን ጉብኝት አስከትለው ሲሆን የአሜሪካዊቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ጉብኝትም እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሶማሊያ የመጀመሪያዋን ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ከመሾሟ ጋር ተገናኝቷል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሦስተኛዋ ሰው የሆኑት አምባሣደር ሼርማን በትናንት የሞቃዲሾ ጉብኝታቸው ወቅት ሼህ ሃሰን ሼህ ሞሐሙድ እና ሌሎችም የመንግሥቱን ከፍተኛ ባለሥልጣናት አነጋግረዋል፡፡

አምባሣደር ዌንዲ ሸርማን
አምባሣደር ዌንዲ ሸርማን

አምባሣደር ሼርማን ሰኞ ዕለት ናይሮቢ ውስጥ ኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አዲሱ የሶማሊያ መንግሥት ያከናወናቸውን ተግባራት ሲያደንቁ “ሃገሪቱ አሁን ተስፋ የመቁረጥ ሳይሆን የብሩህ መፃዒ ጊዜ ሥፍራ ሆና ትታያለች” ብለዋል፡፡

ሼርማን በመግለጫቸው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የመጀመሪያይቱ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚገኙበት መንግሥት በመመሥረታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ቀደም ሲል ለፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው የነበሩት የፑንትላንዷ ፎዚያ ዩሱፍ ሃጂ አደም ለሶማሊያ ሴቶች “አዲስ ዘመን” ባሉት ወቅት ውስጥ በመሣተፋቸው ኩራት የሚሰማቸው መሆኑን ገልፀው ለሹመታቸውም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

አሥር አባላት ባሉበት አዲሱ ካቢኔ ሌላይቱ ሴት ፖለቲከኛ ማርያን ቃሲም አህመድም የልማትና የማኅበራዊ አገልግሎቶች ሚኒስትር ናቸው፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG