በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀሪኬይን ሳንዲ - እጅግ አደገኛው ዝናም አዘል ንፋስ እና ያሳደረው ስጋት


ሀሪኬይን ሳንዲ
በዩናይትድ ስቴትስ በርካታ ግዛቶችን ያዳረሰ እጅግ አደገኛ ዝናም አዘል አውሎ ነፋስ ሀሪኬይን ሳንዲ «Hurricaine Sandy» ከፍተኛ ጉዳት ባስከተለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ አሜሪካውያን የመኖሪያና የንግድ ቤቶቻቸውን ያጥለቀለቀ ጎርፍ እንዴት እንደሚታደጉ፥ የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠባቸው በጨለማ ተውጠው ያደሩ ቀየዎችና ከተሞች ያሉበትን ሁኔታ ለመለወጥ ውሏቸውን ደግሞ በመማሰን ላይ ናቸው።

በሰዓት 150 ኪሎ ሜትሮች በላይ በሰዓት ተምዘግዝጎ የደረሰው የኃይለኛ ዝናምና የአውሎ ነፋስ ማእበል በመንገዱ ላይ ባገኛቸው ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች፥ 50 ሚልዮን ሰዎችን ለጉዳት እንደሚያጋልጥ ነበረው። በንብረት ላይ የሚያደርሰው ውድመት እስከ 3 ቢሎዮን ዶላር እንደሚጠጋ ነው የተገመተው።

አደገኛው ዝናምና ንፋስ ወደ አካባቢዎቹ እየተቃረበ ባለበት ሰዓት ከፍ ያለው ይደርስባቸዋል በተባሉት ግዛቶችና አካባቢዎች ነዋሪ ከሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋር በሰዓቱ ያካሄድነው ቃለ ምልልስ ነበር፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG