በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


Ethiopia's Prime Minister Hailemariam Desalegn, Aug. 24, 2012.
Ethiopia's Prime Minister Hailemariam Desalegn, Aug. 24, 2012.
«ኢትዮጵያ በጋዜጦች» በተሰኘው ሳምንታዊ ፕሮግራማችን የተካተቱት ርእሶች -በኢትዮጵያ የተደረገው ሰላማዊ የስልጣን ለውጥ ሃገሪቱን አስገርሟል ተባለ
- ገንዘብ በኤለክትሮኒክ የመክፈል ተግባር እንዲለመድ ጥሪ ቀረበ እና የኢትዮጵያ አንበሶች በአይነት የተለዩ እንደሆኑ ተገለጸ የሚሉት ናቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት እንደተሰማ ህዝቡ በድሮዎቹ የስልጣን ሽግግሮች የነበሩትን ግጭቶች በማሰብ ተደናግጦ ነበር። አንድ ከፍተኛ የመንግስት ሰራተኛ የሆነ ወጣት "ስለ ሀገሪቱ መሪ ህልፈት እንደተሰማ እናቴ ከቤት እንዳትወጣ ብላኝ ነበር” ማለቱን ክርስቺያን ሳይንስ ሞኒተር ጋዜጣ ላይ የወጣ ጽሁፍ ጠቅሷል።

ይሁንና ይላል ጽሁፉ በመቀጠል የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ካለ ምንም ግጭት በሰላም በሀገሪቱ ምክር ቤት መጽደቁ ዲሞክራስያዊ ለውጥንና አንጻራዊ መረጋጋትን አስመግቧል።

This is Africa የተሰኘው ከፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ጋር የተያያዘው ድረ-ገጽ በበኩሉ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ቢሆንም የተንቀሳቃሽ ስልክና በኤለክትሮኒክ የአከፋፈል ዘዴን በሚመለከት ያላት መሰረተ-ልማት ደካማ ነው። የውጭ መዋዕለ-ነዋይ ፍሰት አያያዝዋም ለቀቅ ማለት ያለበት ጊዜ ደርሷል ይላል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-10-19-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG