በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በገዢው ፓርቲ ውስጥ የተካሄደው የመሪ ለውጥና አንድምታው


አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ
በቅርቡ በኢትዮጵያ በገዢው ፓርቲ ውስጥ በተካሄደው የመሪዎች ለውጥ ዙሪያ የሚያጠነጥን ውይይት ነው።

ተወያዮቹ፥ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የህገመንግስት ጉዳዮች ተባባብሪ ፕሮፌሰር አሰፋ ፍሰሃ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት በኢህአዲግ ውስጥ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይም ሆነ ሌላ አካል “የበላይነት ቦታ ይይዛል፤” የሚል እምነት ያለመኖሩን ሁለቱ ተወያዮች ተናግረው፤

“የአንድ መሪ የስልጣን ዘመን በሁለት ዙር የስራ ጊዜ ብቻ ይወሰናል፤” የሚለውን የፓርቲውን ውሳኔ አዎንታዊ ነው፤» በሚለው ይስማማሉ።

“ጉዳዩ በኅገ መንግስቱም በዚሁ መልኩ መስፈር ይገባዋል፤” ያሉት ዶ/ር ነጋሶ አክለውም፤ ለሃገሪቱ አደገኛ የሆኑ አዋጆች መኖራቸውንና እነዚህም አዋጆች “ይሻሻላሉ፤” ወይም “ይሰረዛሉ፤” ብለው እንደሚጠብቁ፤ ሕዝቡም ይሄንኑ ተስፋ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ በውይይቱ አስረድተዋል።
XS
SM
MD
LG