በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአጥቢያ ኮከብ አቶ አህመዲን መሃመድ ናስር


“ማንበብ ምርጫ አይደለም ግዴታ ነዉ” ይላሉ የቪኦኤ የአጥቢያ ኮከብ እንግዳ አቶ አህመዲን መሃመድ ናስር። አቶ አህመዲን ለአንድ ሃያ ዓመታት አሜሪካ ዉስጥ በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ኖረዉ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ አገር ወዳድ ናቸዉ።


የአሜሪካ ኑሮ ቢመቸኝም ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ለወገኖች ያለኝን የማበርከት አላማ ስላለኝ ነዉ ብለዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያ ዉስጥ በቆዩበት አራት ዓመታት አስር ቤተ መጽሐፍቶችን በሱሉልታ፣ በወልቂጤ፣ በደብረዘይት፣ ደጀን ጎጃም፣ በወልዲያ ወሉ፣ በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለ ከተማና በካራ ቆሬ በነጻ ከፍተዉ ለሕዝብ አበርክተዋል።

“ማንበብ ምርጫ አይደለም ግዴታ ነዉ” አቶ አህመዲን መሃመድ ናስር
“ማንበብ ምርጫ አይደለም ግዴታ ነዉ” አቶ አህመዲን መሃመድ ናስር


ይህንኑ ነጻ አስተዋጽኦ ለማበርከት ደፋ ቀና ሲሉ የገጠማቸዉን የቢሮክራሲ ችግር “ብረር ብረር የሚያሰኝ ነዉ” ነገር ግን በአንድ ወቅት ፕሬዚዳንት ኬኔዲ እንደተናገሩት ”እኛ ካልሆንን ማን? ዛሬ ካልሆነ መቼ?” በሚል መንፈስ ቻልኩት ብለዋል።


አቶ አህመዲን መሃመድ ናስር አሜሪካ በኖሩበት ዓመታት በባንክ ኦፍ አሜሪካ በሂሳብ ሰራተኛነት እንዲሁም በበርክሌይ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በአስተዳደር ክፍል ዉስጥ አገልግለዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG