በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


Boeing 787 Dream liner
Boeing 787 Dream liner
ከአፍሪቃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመሄድ ላይ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካዘዛቸው አምስት ቦምባርዲያ Q-400 የተባሉ በአዲስ መልክ የተሰሩ አይሮፕላኖች አንደኛውን ባለፈው አርብ በቶሮንቶ ካናዳ እንደተረከበ 4-Traders የተባለው ስለ ንግድና አክስዮኖች ጉዳይ የሚጽፈው ድረ-ገጽ ጠቅሷል።

"በአዲሱ ቦምባርዴር Q-400 አሰራራ ደስተኞች ነን። ለአገር ውስጥና ለክላላዊ ደንበኞቻችን ምርጥ አገልግሎት እንድናቀርብ ያስችለናል። ከኢትዮጵያ ወደ Star Allience መረብ የሚዘዋወሩት ተሰፋሪዎችም ከተሻሻለው አይሮፕላን አገልግሎት ይጠቀማሉ" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር-መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ-ማርያም እንዳስገነዘቡ ድረ ገጹ ጠቅሷል።

በ Human Rights Watch የሰብአዊ መብት ቡድን ስለ አፍሪቃ ጉድይ ጥናት የሚያካሄዱት Ben Rawlence ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የውጭ ተባባሪዎችዋ በኢትዮጵያው የስልጣን ሽግግር ወቅጥ ቆም ብለው በማሰብ ገዢው ፓርቲ ወደ ዲሞክራስያዊ ጎዳና እንዲመለስ በህዝባዊ ማህበራትና በፕረስ ላይ የደነገገውን ገደብ በማንሳት የሀግሪቱን ህገ-መንግስት እንዲያከብርና የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ ማበራታታ የሚችሉበት እድል የሚከፍት ነው ማለታቸውን Think AfricaPress ዘግቧል።
AMH-af-Ethiopia_Press-Review-10-5-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG