9/21/12 —
ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሀገሪቱ የተውት ውርስ ግለሰብ መሪዎች ሊመጡና ሊሄዱ ይችላሉ። ስርአቱ ግን ይቀጥላል የሚለው ዘመናዊ መንግስታዊ ስርአት ነው። ይህም በሀገሪቱ ዘመንዝዊ ታሪክ የመጀመርያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ አስችሏል ይላል ስለአፍሪቃ ጉዳይ ምሁራዊ ትንተናዎች በሚያቀርብ African Arguments ድረ-ገጽ ላይ የወጣው የጃላል ዐብደል ላቲፍ ጽሁፍ።
በብሄር-ብሄረሰቦች ፌዳራላዊ አስተዳደር ላይ የተመሰረተው ስርአት መንፈስ አቶ ደሳለኝ ሃይለማርያምን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በመምረጡ ተግባር ላይ በግልጽ ተንጸባርቋል። ከአናሳ ብሄረሰቦች አንዱ በሆነው ወላይታ የተወለዱት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ቦታ ተረክበዋል።
የኢትዮጵያው ህብረ-ብሄር ፌደራላዊ ስርአት ህገ መንግስት የብሄር
ብሄረሰቦች አባላት በክላላዊም ሆነ በማዕከላዊ ደረጃ የስልጣን ድርሻ የሚያገኙበት ዋስትና ይሰጣል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የወላይታ ብሄረሰብ አባል መሆናቸው ራሱ ተለቅ ባሉት ብሄር-ብሄረሰቦች መካከልየስልጣን ሚዛን ለመጠበቅ የሚረዳ ተምሳሌታዊ እርምጃ ነው። ተለቅ ባሉት ክልሎች መካከል ሊኖር የሚችለውን የስልጣን ትግል ያስወግዳል ሲል የጃላል ዐብደል ላቲፍ ጽሁፍ አስምሮበታል።
3.7 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ ረድኤት እንደሚያስፈልጋቸውና ስለ ኢትዮጵያ የወርቅ ሃብት የሚግልጹ ርእሶችም ተካተዋል።