በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያው ፕረዚዳንት መመረጥ የሽግግሩ ሂደት እምርታ ተደርጎ ታየ


Somalia's new president Hassan Sheikh Mahmud
Somalia's new president Hassan Sheikh Mahmud
አዲሱ የሶማልያ ፕረዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሀሙድ በኦፊሴል ስልጣኑን በመረከባቸው ሀገሪቱ ከሁለት አስርተ-አመታት ግጭትና ትርምስ በኋላ
ህጋዊ የሆነ መንግስት ለማግኘት በቅታለች።

አዲሱ ፕረዚዳንት ትላንት እሁድ ቃለ መሐላ በፈጸሙበት ወቅጥ የኢትዮጵፕያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ የተመረጡት ክቡር አቶ ሃይለማርያም ዳሳለኝና ሌሎች ክልላዊ መሪዎች ተገኝተዋል።

"በፊት የጦር አበጋዞች ወይም የጎሳ መሪዎች፣ የድሮ የዚያድ ባሬ ባለስልጣኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እስላማውያን የሚቆጣጠሩት የፖለቲካ ስልጣንና የጸጥታ ፉክክር ነው የነበረው። አሁን ግን ይኽ ተቀይሮ አዲስ ሰው ተመርጠዋል። በህዝባዊ ማህበረ-ሰቦችና በማህበራዊ ሶሽዮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸው አዲስ መሪ አዲስ በተረቀቀው የሽግግር የፖለቲካ ሂደት መሰረት መመረጥቸው አንድ እምርታ ነው ለማለት ይቻላል" ይላሉ አቶ መድሀኔ ታደሰ።

አንጋፋ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ መድሀኔ ታደሰ በምስራቅ አፍሪቃ የጸጥታ ጉዳዮች ለብዙ አመታት ጥናትና ምርምር በማካሄድ እንዲሁም በአማካሪነት ሲሰሩ ቆይተዋል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአፍሪቃ የአመራር ማዕከልና በአፍሪቃ ህብረት አማካሪ እንዲሁም የቦርድ አባል ሆነው ያገለግላሉ።
AMH-af-Somalia-Analysis-9-17-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG