በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መለስ ዜናዊ በአፍሪቃ ስለነበራቸው ሚናና ስላበረከቱት አስተዋጽኦ


አቶ መለስ በሰላም ድርድር፣ በሰላም ጥበቃና በሌሎችም አፍሪቃ ነክ ጉዳዮች ላይ ስለ ነብራቸው አስተዋጽኦ እንዲሁም ስለ-ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አብራርተዋል።

ሟቹ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአገራቸው አልፎ በአጠቃላይ በአፍሪቃ ስለነበራቸው ሚናና ስላበረከቱት አስተዋጽኦ በአፍሪቃና በአለም መሪዎች ተጠቅሷል። ይህን መሰረት በማድረግም የተሰማቸውን ከፍተኛ ሀዘን ገልጸዋል።

በ United States የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን “በመላ አፍሪቃ ያለው እምነት ከታላላቅ መሪዎች አንዱ የሆኑትን ሰው አጣን የሚል ነው”። በርግጥ በዲሚክራሲ ረገድ ገና ብዙ መሰራት ያለበት ጉዳይ ነው” በማለት እንዳጠቃለሉት ተዘግቧል።

አቶ መለስ በሰላም ድርድር፣ በሰላም ጥበቃና በሌሎችም አፍሪቃ ነክ ጉዳዮች ላይ ስለ ነብራቸው አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓብሊክ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽንስ ዋና ዳይረክተር አቶ ጌታቸው ረዳ አብራርተዋል።
AMH-af-PM-Meles-Role-in-Africa-9-10-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG