9-7-12 —
በሳምንታዊው ኢትዮጵያ በጋዜጦች ዝግጅታችን ባለፈው እሁድ ስለተፈጸመው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት ከቀረቡት በርካታ ጽሁፎች ጥቂቶችን እየጠቃቀስን እናቀርባልን። CNN የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተውልደ ገብረማርያምን አነጋግሮ ስለ ኢትዮያ አየር መንገድ የዘገበውንም አሳጥረን እናሰማለን።
በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃ ህብረት ፕረዚዳንትነቱን ቦታ የያዘችው ቤኒን ፕረዚዳንት Boni Yayi “በነበራቸው ራእይ፣ ባሳዩት ብርታት፣ለነጻና የበለገች አፍሪቃ ባካሄዱት ትግል ምክንያት መለስ ዜናዊ ላለፈው አስርተ-አመት አፍሪቃ የምትተማመንባቸው ሃይል ነበሩ” ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥሩ ገቢ ለማግኘት የቻለው በአመርቂው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና በሀገሪቱ ስትራተጃዊ አቀማመጥ ምክንያት ነው። ከቻይና እስከ አፍሪቃ፣ ህንድና ብራዚል ድረስ መስመር ሲሰራ እኛ ልክ ማሃሉ ላይ ነው ያለነው" በማለት እንዳስረዱ CNN ጠቅሷል።