ዋሽንግተን ዲሲ —
ሙኒት መስፍን የሶስት ዘመን ኢትዮጵያዊን ጆሯቸውን ከሚሰጧቸው ባለ ልዩ ቃና ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት ። “ኖሮ ኖሮ “ የሚለውን ሙዚቃዋን በመሰሉ ብርታትን ቀስቃሽ ሙዚቃዎቿ በወጣቶች ዘንድ ንቃትን ፈጥራለች። የኮ/ል ለማ ደምሰውን “ አስታውሳለሁ” ፣የሰይፉ ዮሃንስን “ የከረሞ ሰው” እና የመሳሰሉትን ዳግም ባቀነቀነችነት አፍታ የአረጋዊያንን ትዝታ ቀሰቅሳለች።ህጻናትን እና ህጻንነትን በሚዘክሩ ስረወቿ ደግሞ ከመጪውን ትውልድ ጋር ተዋወቃለች።
የዛሬ ጋቢና መዝናኛ እንግዳ ሙኒት መስፍን አበበ፣ሙዚቃ ለማህበረሳባዊ ለውጥ ለማዋል በተቀረጹ መርሀ ግብሮች ውስጥ ዐቢይ ተሳታፊም ናት።ከሙያዊ ህይወቷ ጋር የተገናኙ ሀሳቦች የሚደመጡበትን መሰናዶ ይዘን ቀርበናል ። መልካም ቆይታ።