በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታዋቂውን አቀናባሪ ህይወት ስለ ቃኘው "የከተማው መናኝ "


.
.

በ42 ዓመቱ ይህችን ምድር የተሰናበተው አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ በለጋ የወጣትነት ዕድሜው በገባበት የሙዚቃ ህይወቱ ከ400 በላይ ሙዚቃዎችን ስለማቀናበሩ ይነገራል፡፡

የተወዳጁን አቀናባሪ የሕይወት ታሪክ በመጽሓፍ መልክ ለአምባቢያን ያቀረበው ወጣት ደራሲ ይነገር ጌታቸው፣ ኤልያስ በስራዎቹ አማካኝነት በተለያየ አመለካከት ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን የሚያስታርቅ የዘመን ምልክት መሆኑን ይገልጻል፡፡

ኢትዮጵያ ካለችበት የፖለቲካ እና ሌሎች ችግሮቿ የምትወጣው ማህበረሰባዊ የሆነ የሞራል መሰረት ላይ መስራት ሲቻል መሆኑን በማመን፣ የሙዚቃ ስራዎቹ በዚህ ላይ እንዲያተኩሩ ይጥር የነበረው ኤሊያስ ለብዙ ወጣቶች ተምሳሌት እንደሚሆንም ደራሲው ይናገራል፡፡

በኤሊያስ ታሪክ ላይ ያተኮረው “የከተማው መናኝ” የተሰኘው መጽሓፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት ችሏል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ኬኔዲ አባተ ከመጽሓፉ ደራሲ ጋር ቆይታ አቅርቦ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል

የታዋቂውን አቀናባሪ ህይወት ስለ ቃኘው "የከተማው መናኝ"
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:18 0:00


XS
SM
MD
LG