በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞውን የሎተሪ አሸናፊ ሚካኤል አጽበሃ ገብሩን በመግደል የተጠረጠሩ መያዛቸው ተነገረ


የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ ያቀናውን ፣የሎተሪ አሸናፊ ሚካኤል አጽብሃ ገብሩን ገድለዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ፡፡የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንዳስታወቁት በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሂሳብ ሰራተኛ የሆነችው ዕጸገነት አንተነህን በመግደል የተጠረጠሩ 3 ተጠርጣዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

በመስቀል ዋዜማ በከተማዎ በተደረገ ድንገተኛ አሰሳ በርካታ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እና ገንዘብ ለመያዝ መቻላቸውን ያከሉት ኮማንደር ፋሲካ ፣አልፎ አልፎ የሚደርሱ ወንጀሎች ቢከሰቱም አሁንም የከተማዎ ደህነት አስጊ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሀብታሙ ስዩም የዚህን ዘገባ ዝርዝር ያስደምጠናል፡፡

ሚካኤል አጽበሃ ገብሩን በመግደል የተጠረጠሩ መያዛቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG