በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስቃይ ምርመራዎች የተፈጸሙበት ‹‹ማዕከላዊ›› ለጎብኝዎች ክፍት ሊደረግ ነው፡፡


ከግራ ወደ ቀኝ አጥናፍ ብርሃኔ፣ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ፣ አቶ ዝናቡ ቱሉ
ከግራ ወደ ቀኝ አጥናፍ ብርሃኔ፣ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ፣ አቶ ዝናቡ ቱሉ

የኢትዮጵያ መንግስት አሰቃቂ የምርመራ ድርጊቶች ሲፈጸሙበት የነበረውን በተለምዶ ‹‹ማዕከላዊ›› ተብሎ የሚታወቀውን ምርመራ ጣቢያ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱሉ ፣ለአራት ቀናት የሚቆየው ጉብኝት ፣ለዓመታት በዚህ ስፍራ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚታሰቡበት ፣ለወደፊቱ የተሻለ አሰራር እንዲፈጠር የሚመከርበት እንደሚሆን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

በማዕከላዊ ሲፈጸሙ በነበሩ አሰቃቂ ድርጊቶች ሰለባ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ጦማሪ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አጥናፍ ብርሃኔ ግን ፣ ስፍራውን ለጉብኝት ክፍት ከማድርግ ባሻገር፣ ለሰብአዊ መብት ጥሰት የሚዳርጉ አሰራሮች መወገድ አለባቸው ሲል ይሟገታል፡፡

ሀብታሙ ስዩም በጉዳዩ ላይ ቀጣዩን አሰናድቷል ፡፡

የስቃይ ምርመራዎች የተፈጸሙበት ‹‹ማዕከላዊ›› ለጎብኝዎች ክፍት ሊደረግ ነው፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG