በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የተሰቀልኩበት ገመድ ተበጥሶ ለወገብ በሽታ ተዳርጌያለሁ" - መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ


መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ
መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ

በሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ለመግለጽ የሚከብድ ግፍ ተፈጽሞብኛል ያለውን በቅርቡ የተፈታውን የአየር ኃይል አብራሪ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን አነጋግረነዋል።

"የተሰቀልኩበት ገመድ ተበጥሶ ለወገብ በሽታ ተዳርጌያለሁ" - መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:52 0:00

የእሥር ቤቶች በሮች ተከፍተው እሥረኞች እየተለቀቁ ነው። ውሣኔው ከተላለፈ አንስቶ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በዐሥር ሺሆች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ከኢትዮጵያ ወህኒዎች ወደ ነፃነት ወጥተዋል።

አብዛኞቹ እሥረኞች በእሥር ቤቶቹ ውስጥ የደረሱባቸውን የሥቃይ ምርመራዎች ዓይነት እየተናገሩ ናቸው።

ኢትዮጵያ ከእንግዲህ እንዲህ ያሉ ዘግናኝ ታሪኮች የማይሰሙባት ሀገር ትሆን ዘንድ ተስፋና ምኞታቸውን ገልፀዋል፤ የሕግ የበላይነት እንዲፀናም ጠይቀዋል።

ጽዮን ግርማ በቀደሙት ሁለት ዘገባዎች ከፍያለው ተፈራና አሸናፊ አካሉ የተባሉ ወጣቶችን አነጋግራ ነበር፤ ለዛሬ ደግሞ በቅርቡ የተፈታውን የአየር ኃይል አብራሪ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን የእስር ቤት ቆይታ ይዛለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG