በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኪነ-ጥበብ ለሰብዓዊነት ፦ቆይታ ከ"ላምባ" ፊልም ደራሲ እና አዘጋጅ አንተነህ ኃይሌ ጋር


በቅርብ ዓመታት ለተመልካቾች ቀርበው ፣ መነጋገሪያ ከነበሩት ፊልሞች መካከል አንዱ ፣"ላምባ" የተሰኘው ፊልም ነው። በኩላሊት ህመም የምትሰቃይ ታዳጊ ወጣትን ህይወት ለመታደግ ቤተሰቧ የሚከፍለውን አሳዛኝ መስዋትነትን ፊልሙ ያስቃኛል ።

የፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጅ አንተነህ ኃይሌ ከፊልም ባለሙያነቱ ባሻገር፣ በኩላሊት ህመም ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ደፋ ቀና የሚል በጎ አድራጊ ነው ። ከአጋሮቹ ጋር ባቋቋሙት የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት የኢትዮጵያዊያንን ህይወት ለማትረፍ የሚያደርጉትን ፈተና የተሞላ ጥረት የተመለከተ የአንተነህን ኪነጥበብን ለሰብዓዊነት ማፍኪያ ከሚጠቀሙ ወጣት ከያኒን መካከል አንዱ ነው-ለማለት ይቻለዋል ።

የፊልም ባለሙያው እና የበጎ ተግባራት አስተባባሪው አንተነህ ኃይሌ በዚህ ዝግጅት በብዙሃን ልብ ስለቀረው "ላምባ " ፊልም እና ዛሬም ድረስ ስለዘለቁት የየኩላሊት ህመምን የተመለከቱ የማስገንዘቢያ እንቅስቃሴዎች ያስረዳናል ።

ኪነ-ጥበብ ለሰብዓዊነት ፦ቆይታ ከላምባ ፊልም ደራሲ እና አዘጋጅ አንተነህ ኃይሌ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:19 0:00


XS
SM
MD
LG