በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጉልበት ሰራተኞች ጀምሮ ስራ ፈላጊዎችን አገናኙ መተግበሪያ


.

"ጉዳይኦን" ከስድስት ወራት በፊት ስራ የጀመረ ስራ ፈላጊና ቀጣሪዎችን አገናኝ አውታር(መተግበሪያ) ነው። ከ15ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስራ ለመቀጠር እና ለመቅጠር እየተጠቀሙበት ስለመሆኑ ፈጣሪዎቹ የሚናገሩለት መተግበሪያ በስልክ ላይ የሚጫን ነጻ አገልግሎት ነው።

ከጉልበት ሰራተኞች ጀምሮ ልዩ ክህሎትን የሚጠይቁ ባለሙያዎች እንዲጠቀሙበት ተደርጎ የተሰረው መተግበሪያ ስራ ለመቀጠር እና ለመቅጠር ያለን አልፊ ሂደት የማስቀረት ዓላማ እንዳለው መተግበሪያውን የሰራው ተቋም ኃላፊ አቶ ዓለም አብርሃ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ለማሳደግ በማሰብ ተቋማቸው ስራ ፈላጊ እና ቀጣሪዎችን የሚያገናኝ የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር ዕቅድ እንዳለው የተናገሩት አቶ ዓለም፣ በሀገር ቤት ያዩት ባለሙያዎችን የማግኘት ውጣ ውረድ ለፈጠራው መነሻ እንደሆናቸው አክለዋል።

ሀብታሙ ስዩም ከአቶ ዓለም አብረሃ ጋር ያደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ።

ከጉልበት ሰራተኞች ጀምሮ ስራ ፈላጊዎችን አገናኙ መተግበሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00


XS
SM
MD
LG