በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ድርድር «ጥቅሜን አስጠብቄያለሁ» አለች


ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጋዜጠኞች ጋር የጥያቄና መልስ መድረክ
ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጋዜጠኞች ጋር የጥያቄና መልስ መድረክ

ከህዳር 5-6 /2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ፣ ከህዳር 22-23/2012  በካይሮ ፣ከታህሳስ 12-13/2012 በካርቱም  ፣ እንዲሁም ከጥር 4/2012 እስከ ጥር 6/2012 ድረስ በዋሺንግተን ዲሲ የተደረጉት እና ታላቁ የህዳሴ ግድብን የተመለከቱ ድርድሮች የኢትዮጵያን ጥቅም ያስጠበቁ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል።

ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጋዜጠኞች ጋር በነበረ የጥያቄ እና መልስ መድረክ ላይ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይሄንን የተናገሩት።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ርምጃ የሚሆነው የቴክኒክ ኮሜቴው አባላት ለስምምነት የመረጧቸውን ጉዳዮች ህጋዊ ቅርጽ እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው ፣ ኢትዮጵያ ከ4-እስከ 7 ዓመት ባለው ጊዜ (እንደ ውሃ ፍሰቱ ሁኔታ) በመገንባት ላይ ያለችውን ግድብ በውሃ ትሞላለች ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በመጪው ሁለት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከግድቡ "የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ትጀምራለች" ብለዋል።

ሁለቱ ባለስልጣናት የአሁኑ ድርድር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ጥቅም ያስጠበቀ መሆኑን ደጋግመው ከማንሳት አልፈው ለታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የሚኖረውን ጠቀሜታም አብራርተዋል።

አጠር ያለውን የድምጽ ዘገባ ያድምጡ:-

ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት ስራ ከ4- 7 ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ አቅዳለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG