በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ቀጣዩን ምርጫ ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ ለማድረግ ምን ያህል ዝግጁ ናት?


ምርጫ 2007/ፋይል
ምርጫ 2007/ፋይል

"የባለፈውን ምርጫ ብናስታውስ..." ይላሉ ቀደም ባሉ ዓመታት በኢትዮጵያ የተደረጉ ምርጫዎች ለአካል ጉዳተኞች የተመቹ እንዳልነበሩ ለማስረዳት ማሳያዎችን ያከታታሉት የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን የቦርድ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ ። የበለጠ ማሳያ ይሆን ዘንድ ወደ 1997 ዓመተ ምህረቱ ምርጫ ይመለሳሉ ፣"የቅንጅት አርማ የነበረው ምልክት በምልክት ቋንቋ ደግሞ ሌላ ቋንቋ ነበረው።በዚያ ምክንያት ብዙ መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን በ97 ዓመተ-ምህረት በተፈጠረው የምርጫ ግርግር ወቅት ተጎድተዋል።እነሱ ቋንቋቸው ስለሆነ የተጠቀሙበት ምልክት ከፖለቲካው አርማ በመመሳሳሉ ትልቅ ተግዳሮት ያጋጠመበት ሁኔታ ተፈጥሯል" ሲሉም ያስረዳሉ።

የዘንድሮው ምርጫ ግን በምርጫ ጣቢያ መረጣ፣ለምርጫ በሚውሉ ቁሳቁሶች አጠቃቀም ብሎም በአጠቃላይ በምርጫ አፈጻጸም ሂደት ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ እንዲሆን ፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጋር ምክክር ጀምሯል።

ሙሉ ጥንቅሩን ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ ምርጫ ለማድረግ ምን ያክል ዝግጁ ናት?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG