በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው የበይነ-መረብ ገበያ በድሮን ሸቀጦችን ለማድረስ እየተሰናዳ መሆኑን አስታወቀ


.
.

በይነ-መረብን መሰረት ያደረገ ግብይትን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፋት ጥረት እያደረጉ ካሉ ድርጅቶች አንዱ አዲስ መርካቶ ነው።ከተቋቋመ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ድርጅቱ በበይነ- መረብ ላይ ገበያው በኩል ሸቀጦችን ይሸጣል ፣ ደንበኞች በሚገኙበት ስፍራ የየብስ ትራንስፖርት በመጠቀም ያደርሳል።

ድርጅቱ በጥቂት ወራት ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ሸቀጦችን የማድረስ አገልግሎት ለመጀመር እየተሰናዳ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አቢይ መባ ስላሴ ለአገልግሎቱ የተመረጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እስከ 4 ኪሎግራም የሚመዝን ሸቀጥ መሸከም የሚችሉ እንደሆኑ ፣አርባ ደቂቃ ይወስድ የነበረን የማድረሻ ሰዓት ፍጆታ ወደ ስምንት ደቂቃ ዝቅ ማድረግ እንደሚችሉም አክለዋል።

ድሮኖቹ ደንበኞች ወደ ሚገኙባቸው ሰፈሮች በመብረር የተላከውን ሸቀጥ እንደሚያደርሱም ተናግረዋል።

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ።

ኢትዮጵያዊው የበይነ-መረብ ገበያ በድሮን ሸቀጦችን ለማድረስ እየተሰናዳ መሆኑን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:53 0:00


XS
SM
MD
LG