በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱሪዝም ኢትዮጵያ የጎብኝዎችን ቁጥር የሚጨምሩ አዳዲስ ስልቶችን መቅረጹን አስታወቀ


 የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሃላፊ አቶ ስለሺ ግርማ
የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሃላፊ አቶ ስለሺ ግርማ

የዐይን እና የመንፈስ መስህቦች መናገሻ የሆነችውን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከመላው ዓለም በእየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሀገር ጎብኝዎች ይተማሉ።ከጎብኝዎች የሚገኘው ገቢ ከሀገር ውስጥ ምርት ምጣኔ (GDP) 5 በመቶውን በመሸፈን የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት እየደገፈ የዘርፉ ባለስልጣናት ይናገራሉ።

ይሄን በረከቱን የተረዳችው ኢትዮጵያ ፣ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ «ቱሪዝም ኢትዮጵያ» የተሰኘ ፣ የቱሪዝሙን ዘርፍ በልዩ ሁኔታ የሚከታታል ተቋም ከመሰረተች ሰነባብታለች።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ሃላፊ የሆኑትን አቶ ስለሺ ግርማ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንደተናገሩት ተቋማቸው አሁን ላይ ደግሞ የጎብኝዎችን ብዛት ለመጨመር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ሁለት አዳዲስ ስልቶችን መተግበር ጀምሯል።

ከዚህ በተጨማሪ የጎብኝዎች ፍሰት የሚጨምርባቸውን የታህሳስ እና ጥር ወራት ካለ ጸጥታ ችግር ለማሳለፍ ከአጋዥ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር መስራት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ሀብታሙ ስዩም ያስደምጠናል።

ቱሪዝም ኢትዮጵያ የጎብኝዎችን ቁጥር የሚጨምሩ አዳዲስ ስልቶችን መቅረጹን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG