በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሄርን መሰረት ያደረገ እስር እና እንግልት እንዳልፈተጸመ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ


አዲስ አበባ ፖሊስ መለዮ
አዲስ አበባ ፖሊስ መለዮ

በአዲስ አበባ ከተማ "ብሄርን መሰረት ያደረገ እስር አልተከናወነም" ሲል የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ። በከተማዋ በተለይ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እስር እና እንግልት ተንሰራፍተዋል የሚሉ ክሶችን መሰረት አድርጎ ቪኦኤ -ጥያቄ ያቀረበላቸው የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ፣በቁጥጥር ስር ያሉት ግለሰቦች በሽብርተኝነት ከተፈረጁት ህወሐት እና ሸኔ ስምሪት ወስደው የጸጥታ አደጋ የደቀኑ እንደሆነ ተናግረዋል ።

ጉቦ የሚቀበሉ ፖሊሶች ስለመኖራቸው መስማታቸውን የገለጹት ኮማንደር ፋሲካ ፣ በጥቂቶች አድራጎት ምክንያት ግን ትልቅ መስዋትነት እየከፈለ ነው ያሉት ፖሊስ ኃይል የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰለባ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ለእስር እንደታዳረጉ መግለጻቸው ይተወሳል።

ሙሉ ዘገባውን ሀብታሙ ስዩም ያሰማናል ።

በአዲስ አበባ ብሄርን መሰረት ያደረገ እስር እና እንግልት እንዳልፈተጸመ ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

XS
SM
MD
LG