ዋሽንግተን ዲሲ —
የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንደተናገሩት ፣ከቅድመ- መደበኛ ትምህርት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚደርስ የትምህርት አሰጣጥ እና አወቃቀር ለውጦች ይደረጋሉ፡፡
እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣በአዲሱ ማሻሻያ ነባሩ የአጠቃላይ ትምህርት ርከን ተቀይሯል፡፡በዚህም መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ከ1ኛ-እስከ 6ኛ ክፍል፣የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ከ7ኛ-8ኛ፣የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል እንዲሆን ታቅዷል፡፡
ቀድሞ ይሰጥ የነበረው የ10ኛ ክፍል "ወደ መሰናዶ ትምህርት መግቢያ" ሀገራዊ ፈተና ቀሪ እንዲደረግ መወሰኑንም ተናግረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጥ ትምህርትን፣የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አደረጃጀትን፣የመምህራን ትምህርት ዝግጅትን የሚመለከቱ ማሻሻያ እና ለውጦችን ይፋ አድርገዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከስር የሚገኘውን መዳረሻ በመጫን ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ