በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶችና የሚደርሱባቸው ጾታዊ ጥቃቶች


ወ/ሮ አስቴር ይልማ በዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ግዛቶች ፤ በተለይም በኒውዮርክ እና በኒውጀርሲ ግዛቶች የፍርድ ቤቶች ዋና አስተርጓሚ በመሆን ከ17 ዓመት በላይ አገልግላለች፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የአስተርጓሚዎች ማህበር ፣ የብሄራዊ የህግ አስተርጓሚዎች ማህበር እና የኒውዮርክ የአስተርጓሚዎች ክበብ አባል ናት፡፡

በስነ-ልቦና ጥናት (በሳይኮሎጂ) የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በቴሌቪዥን ትርኢት ዝግጅት አሶሺየት ዲግሪ እና በቤት ውስጥ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎችን የማማከር (አድቮከሲ) የምስክር ወረቀት አላት፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ከሰላሳ ዓመት በላይ ከሱስ ጋር የተገናኙ ጥናቶችን አድርጋለች፡፡ የ‘ላም አለኝ’ አማርኛ ፊልም ተባባሪ አዘጋጅም ናት፡፡

ከአምስት ዓመት ወዲህ ጀምሮ የቤት ወስጥ ጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎችን የማማከር አገልገሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡

ወ/ሮ አስቴር ይልማ በዩናይትድ ስቴትስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ዘንድ እየደረሱ ስላሉ የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ድምጿ ኤደን ገረመው ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:37 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG