በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ ፣ በረድዔት አቅርቦት ችግር ምክንያት ሊቋረጥ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በምህጻሩ ኦቻ ፣በይዞታው ያሉ ቁሳቁሶች መመናመናቸውን ተከትሎ ፣ የጦርነት አውድማ ሆኖ በሰነበተው የሰሜን ኢትዮጵያው ትግራይ ክልል የነበረውን ሰብዓዊ ድጋፍ የማዳረስ ተግባር እንዲያቆም ሊገደድ እንደሚችል አስታውቋል ።
በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ከባድ ጦርነት እርዳታ ፣ከአውሮፓያዊኑ ታህሳስ አጋማሽ ወዲህ ለችግር ለተዳረጉ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች እንዳይደርስ ከልክሏል ።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጄንስ ሊያርኪ ፣ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች የግል የረድኤት ተቋማት ፣ በከፋው በረድኤት ቁሳቁሶች ፣ነዳጅ እና ገንዘብ እጥረት ምክንያት እንቅስቃሴያቸውን ቀደም ባለው ጊዜ ለመቀነስ መገደዳቸውን ተናግረዋል ።
“ተቋማቱ ፣ እንቅስቃሴያቸውን (በአውሮጳዊያኑ) የካቲት ወር ሙሉ በሙሉ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል “ ያሉት ሊያርኪ ፣
"ለተጨማሪ የምገባ መርሀ ግብር ብሎም የከፋ አጣዳፊ የምግብ እጥረትን የሚፈጥራቸው ችግሮችን ለማከም የሚያስፈልጉ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ቀድሞውኑ አልቀዋል ” ብሏል ።
የዓለም የምግብ መርሐ ግብር 13 በመቶ ፣ከ5 ዓመት በታች የሆኑ የትግራይ ህጻናት እንዲሁም ከነፍሰጡሮች እንዲሁም ፣ እመጫት እናቶች መካከል ግማሹ በከፋ የምግብ እጥረት መጎሳቆላቸውን ጠቅሶ፣ ሁኔታው በበሽታ የመያዝን እንዲሁም ለሞት መዳረግን የሚጨምር እንደሆነ ጠቁሟል ።
ከቀናት በፊት የነደጅ ክምችት መንጠፉን ተከትሎ ፣ የረድዔት ሰራተኞች የቀረውን ድጋፍ በእግራቸው እየተዟዟሩ ለማደረስ መጣራቸውን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ፣ በአንጻሩ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሰብኣዊ ድጋፍ ስርጭትን ለማዳረስ መቻላቸውን እና ወደ 380ሺ ሰዎች የምግብ እደላ አካል እንደሆኑ ተናግረዋል ።
በቅርቡ ወደ ትግራይ በአውሮፕላን ሰብዓዊ ድጋፍ የማዳረስ እርምጃ መጀመሩን ተከትሎ የድጋፉ መጠን ከፍ ማለት መጀመሩን ያወሱት ሊያርኪ ፣ ለሁኔታው የሚያስፈልገውን ከፍ ያለ መጠን ያለው ድጋፍ ግን በአውሮፕላን ብቻ ማጓጓዝ እንደማይቻል ተናግረዋል ።