በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ ፈንቅል ትግራይ የወጣቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ፣ ቆይታ ከአቶ የማነ ንጉስ ጋር


.
.

የትግራይ ህዝብ ያቀረባቸው ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ባለመሆኑ ፣በክልሉ የሚገኘውን የህወሐት ዓመራር በተለያዩ የትግል ስልቶች ለመለወጥ ያለመ የወጣቶች እንቅስቃሴ ጥረት እያደረገ መሆኑን የእንቅስቃሴው ሊቀመንበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቁ።

“ፈንቅል ትግራይ” የተባለው እንቅስቃሴ ሊቀመንበር አቶ የማነ ንጉስ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ -የትግራይ ህዝብ ትግል በህዋዕት ጥቂት የቡድን ስብስብ ተጠልፏል ሲል ወቅሰዋል።

የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አማኑኤል አሰፋ በበኩላቸው “ፈንቅል ትግራይ” በሚል የሚንቀሳቀሰው ቡድን በፌዴራል መንግስት ድጋፍ የተቋቋመ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ያለመ ቡድን ነው በሚል የአጸፋ ወቀሳ ሰንዝረዋል። የዚህ ቡድን አባላት የትግራይን ክልል መቼም እንደማይዙ፣ ተይዘውም የህግ የበላይነት ሊረጋገጥባቸው እንደሚችል አስጠንቀቀዋል።

ሀብታሙ ስዩም ሁለቱንም ገጾች አነጋግሯል። በመጀመሪያ ከፈንቅል ትግራይ ሊቀመንበር አቶ የማነ ንጉስ ጋር ያደረገው አጭር ቆይታ ይሰማል።

የትግራይ ህዝብ ትግል በህወሐት ተጠልፏል ሲል “ፈንቅል ትግራይ ’’ ወቀሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:04 0:00


XS
SM
MD
LG