ዋሽንግተን ዲሲ —
በአገልግሎት ሰጪ፣ በግንባታ ስራ፣ በማዕድን ቁፋሮ መስኮች በተሰማሩ ድርጅቶች እንዲሁም መካከለኛ እና ትላልቅ የንግድ ተቋማት ላይ ባከናወንኩት የናሙና ጥናት አዳዲስ እና የተሻሻሉ ግኝቶችን (ኢኖቬሽኖችን) የሚጠቀሙት ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑን ደርሸበታለሁ ሲል የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ሁለተኛውን ሀገር አቀፍ የኢኖቬሽን ጥናት ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው ኢንስቲትዩቱ የናሙና ጥናት ካደረገባቸው ድርጅቶች እና ተቋማት መካከል 19.4 በመቶው ብቻ ዘመናዊ የምርት ሂደት፣የገበያ ብልሃቶች እና ተቋማዊ አደረጃጀትን የመሰሉ ዘመነኛ ግኝቶች (ኢኖቬሽኖችን ) ተግባራዊ እያደረጉ እንደሆነ አስታውቋል።
ሀብታሙ ስዩም በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ተመራማሪ ወደ ሆኑት ዶ/ር ጀማል መሐመድ በመደወል ስለ ጥናቱ ተጨማሪ ማብራሪያ አግኝቷል።