በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ

በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለመጣው የምግብ ዋስትና እጦት የ17 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊዝስ አስታወቁ። አዲስ የተመደበው ይህ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ለተጨማሪ አደጋ ያጋለጠው ‘ኤልኒኞ’ የአየር መዛባት ያስከተለው ድርቅ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የከፋ ጉዳት ሊያስከትል መቻሉ ያሳደረውን ብርቱ ስጋት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያን የገጠመው የምግብ ዋስትና እጦት በመጭው ወራትም እየበረታ ሊሄድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ከሐምሌ እስከ መስከረም ባሉት የክረምት ወራት ውስጥ በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከዚህ ቀደም የተከሰተው ድርቅ እና በሃገሪቱ ያሉት ግጭቶች አሁንም ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ቀጥለዋል። በሌላ በኩል የጎርፍ መጥለቅለቅ ተጨማሪ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከ2013 እስከ 2015 ባለው ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ጨምሮ በሃገሪቱ በተከታታይ ለደረሱ ምስቅልቅል ሁኔታዎች የተጋለጡ ማሕበረሰቦችን ከገጠማቸው የከፋ ጉዳት ለመታደግ ያለው ዕድል አጭር ዕድሜ ዘላቂ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እያሻቀበ ላለው የተረጂዎች ቁጥር ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

በኢትዮጵያ ለተረጂዎች የምግብ ርዳታ ለማቅረብ 3ነጥብ4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቁ። የተረጅዎች ብዛት በተያዘው ዓመት 10ነጥብ4 ይደርሳል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ አታለለ አቡሃይ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የተረጅዎች ብዛት 6ነጥብ6 ሚሊዮን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በጎርፍ እና በሌሎችም ምክንያቶች ይኸው አኀዝ እንደሚጨምር ባለሞያው አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG