እስኪ ይሞክሩት
ማክሰኞ 10 ሴፕቴምበር 2024
ሌኦናርዶ ዳ ቪንቺ ሞና ሊሳን ያጠናቀቀው በ1496-1497 ዓ.ም. እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሞና ሊሳ “ላ ጆኮንዳ“ ተብላም ትጠራለች፡፡ ሞና ሊሳ ያኔ በፍሎረንስ እጅግ የናጠጠ ከበርቴ የነበረ ፍራንቼስኮ ዴል ጆኮንዳ ሚስት የሊሳ ጌራርዲኒ ምስልም እንደሆነ ይነገራል፡፡ (ለነገሩ ሌሎች ብዙ አነጋጋሪ የመላ ምት ሃሣቦች አሉ፡፡) ሞና ሊሳን ዛሬ ሰዎች “እጅግ የተዋበች፤ የቁንጅና ቁንጮ” ለማለት ያህል ቢጠቀሙበትም - ነጭ ትርጉሙ “አንድ ፊት” ማለት ነው - በጣሊያን አፍ፡፡