በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

ማክሰኞ 18 ጃንዩወሪ 2022

Calendar
ጃንዩወሪ 2022
እሑድ ሰኞ ማክሰ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ ቅዳሜ
26 27 28 29 30 31 1
2 3 4 5 6 7 8
9 10 11 12 13 14 15
16 17 18 19 20 21 22
23 24 25 26 27 28 29
30 31 1 2 3 4 5
ለቦረና ዞን አርብቶ አደሮች ድጋፍ

በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከብቶታቸው በድረቅ እየተሞቱባቸው ለሚገኙ በኦሮምያ ክልል ለቦረና ዞን አርብቶ አደሮች ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን የዞኖቹ ባላሥልጣናት ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።

የጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ አስተዳድር ከ10 ሺህ በላይ ከብቶችን ተቀብለው ድጋፍ እያደረገ እና በግጦሽ መሬት አሰማርቶ እየተመገቡላቸው መሆኑን አስታውቋል።

በክልሉ የጋሞ ዞን ደግሞ ከ195 ሺህ በላይ ቶን መኖ ማቅረቡን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ተናግረዋል።

የቦረና ዞን ምክትል አስተዳድሪ አቶ አብዲሰላም ዋሪዮ ከ100 ሺህ በላይ ከብቶች በድርቅ መሞታቸውን ገልፀው ለተደረግው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

ከብቶታቸው በድርቅ እየተሞቱባቸው ለሚገኙ አርብቶ አደሮች ድጋፍ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:20 0:00


በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ የሞቱ እንስሳት ቁጥር 160 ሺ መድረሱን ክልሉ አስታወቀ።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ የሞቱ እንስሳት ቁጥር 160 ሺሕ መድረሱን ክልሉ አስታወቀ።

ክልሉ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ልዩ ልዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችም ለድርቁ ተጎጂዎች በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን ክልሉ አስታውቋል።

"አሁን የሀገሪቱ ትኩረት ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ስለተመለሰ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለድርቁ ተጎጂዎች ትኩረት እንዲሰጡ" ሲል ክልሉ ጠይቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

በሶማሌ ክልል ድርቅ የሞቱ እንስሳት ቁጥር 160 ሺሕ ደርሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG