በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ መስከረም ውስጥ የተጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉና ለስድስት ተከታታይ ወራት እርጥበት በመጥፋቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቁጥራቸው የበዛ ከብቶችን መጨረሱን የክልሉ ግብርና ፅህፈት ቤት የእንስሣት ኃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።