የፕሮግራሞች ዝርዝር
የፕሮግራሞች ዝርዝር
ከሰኞ እስከ ዓርብ በየዕለቱ ለግማሽ ሰዓት ከምንሰጠው ዜና፣ እንዲሁም የዕለቱ ዜናዎች ዝርዝርና ትንታኔ በተጨማሪ በቀሪው ግማሽ ሰዓት ወቅታዊ ሁኔታዎች በጥልቀት የሚታዩባቸው ሣምንታዊና መደበኛ ፕሮግራሞች እየተዘጋጁ ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፤ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፤ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፤ ንግድና ምጣኔ ኃብት፤ ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፤ ሴቶችና ቤተሰብ፤ እንዲሁም በየአሥራ አምስት ቀኑ እየተፈራረቁ “ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ” እና “አሜሪካና ሕዝቧ”
ሐሙስ፡- ባሕልና ኅብረተሰብ፤ ሕይወት በቀበሌ፤ እንዲሁም በየአሥራ አምስት ቀኑ እየተፈራረቁ “የተፈጥሮ አካባቢ” እና “ሣይንስና ሕይወት”
ዓርብ፡- እሰጥ አገባ፤ አፍሪካ በጋዜጦች፤ እንዲሁም “አጥቢያ ኮከብ / የማኅበረሰብ ጀግኖች” እና “ለጥያቄዎ መልስ”
ቅዳሜ፡- “የሪፖርተሮች ውይይት / የውይይት መድረክ” እና “ለጥያቄዎ መልስ” በየአሥራ አምስት ቀኑ እየተፈራረቁ፤ እንዲሁም በየሣምንቱ “የሙዚቃ ቃና” ይቀርባሉ፡፡
ዕሁድ፡- “ራዲዮ መፅሔት” እና የዕሁድ ልዩ የመዝናኛና መረጃ ዝግጅት “ቪኦኤን ልስማ” በየአሥራ አምስት ቀኑ እየተፈራረቁ ይተላለፋሉ፡፡
ጋቢና ቪኦኤ
ጋቢና ቪኦኤ በወጣቶች ላይ ያተኮረ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ በአማርኛ የሚተላለፍ የመረጃና የመዝናኛ ሥርጭት ነው፡፡ ጋቢና ቪኦኤ ከሰኞ እስከ ዓርብ በየዕለቱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ለግማሽ ሰዓት ይተላለፋል፡፡ የጋቢና ቪኦኤ ዋና ሃሣብ ወጣቶች መረጃ እንዲደርሣቸው፤ ከዘመኑ ወይም ከመጨረሻ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶች ጋር እንዲተዋወቁ ማድረግ፤ ምርታማና እራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ሊያደርጋቸው የሚችል ሂደትና ሃሣቦች አካል እንዲሆኑ ማገዝ ነው፡፡