በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራዲዮ ሞገዶች

የራዲዮ ሞገዶች

ቪኦኤ24 (VOA24)

ቪኦኤ24 (VOA24) ከአሜሪካ ድምፅ ወደ ኢትዮጵያ የሚሠራጩ የፎቶግራፎችና የድምፅ መረጃዎችን ከናይልሳት የሚያገኙበት የሳተላይት መሥመር ነው፡፡ ቪኦኤ24ን በሣተላይት መልዕክት መቀበያዎ ላይ ለማግኘት ከዚህ ሥር ያሉትን አድራሻዎች ይከተሉ፡-

ሳተላይት ፡- ዩተልሳት 7 – 7 ዲግሪ ምዕራብ / 353 ዲግሪ ምሥራቅ ላይ ትገኛለች፡፡

ትራንስፖንደር፡- ኢ36

ዲ/ኤል (ዳውን ሊንክ) ፍሪኴንሲ ወይም ሞገድ፡- 12.399GHz (ጊጋ ኸርትዝ)

ኤፍኢሲ፡- 5/6

ሲምበል ሬት፡- 27.5 MSym/s

ዲ/ኤል ፖላራይዜሽን፡- ቨርቲካል (V)

ቨርቹአል ቻናል፡- 4132 (VOA24 Pic w/Audio) - ምሥልና ድምፅ ለማግኘት

የቪኦኤ መደበኛ ሥርጭቶች የአየር ሞገዶች

የቪኦኤን የራዲዮ ሥርጭት በአማርኛ በሣምንት ሰባት ቀን በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3፡00 ስዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ወይም በለንደን ዓለምአቀፍ ሰዓት አቆጣጠር ከ1800 እስከ 1900 ሰዓት፤ ከመጋቢት 2008 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2009 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚያገኙባቸው የአጭር ሞገድ ጣቢያዎች ከዚህ ሥር የሠፈሩት ናቸው፡፡

19 ሜትር ባንድ በ15630 ኪሎ ኸርትዝ

22 ሜትር ባንድ በ13860 ኪሎ ኸርትዝ

25 ሜትር ባንድ በ12040 ኪሎ ኸርትዝ

25 ሜትር ባንድ በ12080 ኪሎ ኸርትዝ

25 ሜትር ባንድ በ12140 ኪሎ ኸርትዝ

የጋቢና ቪኦኤ ፕሮግራም የአየር ሞገዶች

ከሰኞ እስከ አርብ በየዕለቱ ከምሽቱ 1 ሰዓት ተኩል እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የአሜሪካ ድምፅ “ጋቢና” በሚል ርዕስ በአማርኛ የሚያስተላልፈውን ሥርጭት በአጭር ሞገድ ከታች በተቀመጡት ጣቢያዎች ላይ ይከታተሉ፡፡

49 ሜትር ባንድ 6080 ኪሎ ኸርትዝ

19 ሜትር ባንድ 15580 ኪሎ ኸርትዝ

ተጨማሪ ሥርጭት

ከሰኞ እስከ አርብ በየዕለቱ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል የሚሠራጨውንም ዝግጅት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG