በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቴክኒክ ድጋፍ

የቴክኒክ ድጋፍ

ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

ከሳይታችሁ ድምፅ መስማት እንዴት እችላለሁ?

አብዛኞቹ የድምፅና የምሥል ማጫወቻዎች በቪኦኤ ዌብ ሳይት ላይ ይሠራሉ፡፡ ኮምፕዩተርዎ በአግባቡ የተዘጋጀና ተፈላጊ ሁኔታዎችን ያሟላ ከሆነ MP3 የኦዲዮ ፋይሎቻችንን በአብዛኞቹ የድምፅ ማጫወቻወችዎ መስማት መቻል አለብዎ፡፡ የሚጠቀሙት ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ከሆነ ዊንዶውስ ማጫወቻ አብሮ ተጭኗልና ሊከፍቱትና ሊያጫውቱበት ይችላሉ፡፡ ዊንዶውስ ሚድያ ፕሌየር 9 እና ከዚያ በኋላ የወጡ ማጫወቻዎችን ቢጠቀሙ ይመከራል፡፡ እርስዎ የሚመርጡት ሪል ፕሌየርን ከሆነ ደግሞ 10 እና ከዚያ በኋላ የወጡትን ማጫወቻዎች ይጠቀሙ፡፡ ማንኛውንም የኦዲዮ ወይም የድምፅ ፋይል ኮምፕዩተርዎ ላይ መስማት ከፈለጉ ማጫወቻው ሊኖርዎ ይገባል፡፡ ሪል ፕሌየርን ወይም ዊንዶውስ ሚድያ ፕሌየርን በፈለጉ ጊዜ መጫን ይችላሉ፡፡ ማጫወቻዎቹን ለመጫንና ለማረቅ፤ እባክዎ በየራሳቸው ዌብሳይቶች ላይ የተቀመጡትን የአጫጫንና የማስተካከያ መመሪያዎች ይከተሉ፡፡

አንድ የድምፅ ማገናኛ ተጭኜ ድምፁ ካልተጫወተ ምን ማድረግ አለብኝ?

የድምፅ ማጫወቻዎ ያላረጀ ከሆነና የሚጠበቁበትን የባንድዊድዝ የቴክኒክ መሥፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ በቀጥታ የሚጫወቱ የድምፅና የምሥል ፋይሎችን ከመጫወት ሊከላከል የሚችለውን ማገጃ ወይም ፋይርዋል ማረቂያቃቹ /ሴቲንግስ/ ውስጥ ገብተው ማስተካከልና እንዲያሳልፍ መፍቀድ ይኖርብዎታል፡፡

በነገራችን ላይ ይህ ችግር ሊፈታ የሚችለው በአጠቃላይ መፍትኄ ሳይሆን በተናጠል፤ እንደየችግሩ ሁኔታና ቦታ ነው፡፡ ችግሩ ባጋጠመዎ ጊዜ ያሉት ሥራዎ ቦታ ወይም ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ከሆነ የቴክኒክ አጋዥ ባለሙያውን እርዳታ ይጠይቁ፡፡

በትኞቹ የኢንተርኔት መፈለጊያ /ብራውዘሮች/ ነው እናንተ የምትጠቀሙት?

‘VOANews.com’ን በማንኛውም መፈለጊያ ላይ ሆነው መክፈትና መግባት ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዌብ ሣይታችንን የምንሠራው ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 7.x እና ሞዚላ ፋይርፎክስ 1.x ወይም 2.x ላይ ነው፡፡

ቪኦኤን ዋናው መነሻ ገፄ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

‘ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 6 ፎር ዊንዶውስ’ /Internet Explorer 6 for Windows/ እና ከዚያም በኋላ የወጡ /or higher/ መፈለጊያዎች /ብራውዘሮች/ ላይ ሆነው ከTools ሜኑ Internet Options የሚለውን ይምረጡ፤ በሚከፈተው መስኮት ላይ General የሚለው ተከፍቶ ይመጣልዎታል፡፡ Home page በሚለው ክፍል ውስጥ Address የሚል ሲያዩhttp://www.voanews.com ብለው ይፃፉና በመስኮቱ ግርጌ ያለውን ‘Ok’ የሚለውን ይጫኑ፡፡

‘ፋየርፎክስ 2.x ፎር ዊንዶውስ’ /Firefox for Windows 2.x/ ላይ ከሆኑ ከTools ሜኑ Options የሚለውን ይምረጡ፤ Home Page: የሚለው ሣጥን ውስጥhttp://www.voanews.com ብለው ይፃፉና በመስኮቱ ግርጌ ያለውን ‘Ok’ የሚለውን ይጫኑ፡፡

ማክንቶሽ /MacOS X/ ላይ ከሆኑ ከTools ሜኑ Options የሚለውን ይምረጡ፤ Home Page: የሚለው ሣጥን ውስጥ http://www.voanews.com ብለው ይፃፉና በመስኮቱ ግርጌ ያለውን ‘Ok’ የሚለውን ይጫኑ፡፡

እነዚህን አድርገው አሁንም ችግር ካጋጠመዎ፤ እባክዎ ለተጨማሪ እርዳታ ኢሜል ያድርጉልን፡፡

XS
SM
MD
LG