በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአጠቃቀም ደንብና የግል ገመና ጥበቃ ፖሊሲ

የአጠቃቀም ደንብና የግል ገመና ጥበቃ ፖሊሲ

የግል ገመና መረጃ ማስታወሻ

እርስዎ የግል ገመናዎን ወይም የማንነትዎን መግለጫ መረጃ ለመስጠት እስካልፈለጉ ድረስ ዌብሳይታችንን ሲጎበኙ የግል መረጃዎችዎን ጨርሶ አንወስድም፡፡

በቀጥታ የሚወሰዱና የሚቀመጡ መረጃዎች

ዌብሳይታችንን እየጎበኙ ሳሉ ገፆችን ከማንበብ፣ ወይም መረጃ ከኢንተርኔት ከማውረድ በስተቀር ሌላ ነገር ካልሠሩ ስለ ጉብኝትዎ የምንሰበስበው የተወሰነ መረጃ ነው፡፡ ይህ መረጃ ደግሞ በግል የእርስዎን ማንነት የሚመለከት አይደለም፡፡

ስለጉብኝትዎ በቀጥታ የምንሰበስበውና የምንይዛቸው መረጃዎች የሚከተሉት ብቻ ናቸው፡-

1. የሚገኙበትን የኢንተርኔት ግንኙነት ማንነት እንወስዳለን፡፡ ለምሣኔ ከሥራዎ ቦታ ከሆነ ወይም የግልዎ የኢንተርኔት አካውንት ከሆነ ወይም ከትምህርት ቤትዎ ወይም ዩኒቨርሲቲዎ ከሆነ፤ እንዲሁም እየተጠቀሙ ያሉበትን ኮምፕዩተር የኢንተርኔት አድራሻ (አይፒ አድራሻ - IP ADDRESS) እንይዛለን፡፡ አይፒ አድራሻ ወደ ኢንተርኔት በገቡ ጊዜ ሁሉ ለእርስዎ ኮምፕዩተር የእርስዎ ፍቃድና ተሣትፎ ሳይጠየቅ የሚሰጥ ቁጥር ነው፡፡

2. ወደ እኛ ዌብሳይት ለመግባት የተጠቀሙበት መፈለጊያ ወይም ብራውዘር እና የተጠቀሙበት ኦፐሬቲንግ ሲስተም (ዊንዶውስ/ኦኤስ..)

3. ወደ ዌብሳይታችን የገቡበት ቀንና ሰዓት

4. የጎበኙት ገፅ

5. ወደ እኛ ዌብሳይት የገቡት ከሌላ ዌብሳይት በማገናኛ ተመርተው ከሆነ የዚያኛውን ዌብሳይት አድራሻ እንመዘግባለን፡፡

የግል መረጃዎችዎን ከላኩልን

ኢሜል ልከውልን ወይም ዌብሳይታችን ላይ የሚገኝ ቅፅ ከግል መረጃዎችዎ ጋር ሞልተው በማስገባት መረጃዎችዎን ሊሰጡን ከመረጡ ለመልዕክትዎ መልስ ለመስጠት ወይም የጠየቁትን መረጃ ለእርስዎው መልሰን ለመላክ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ለሌላ ለምንም ጉዳይ ማንነትዎን የሚመለከቱ መረጃዎችን አንሰበስብም፡፡

ከዚያ ውጭ እርስዎ በሰጡን ወይም በላኩልን የግል መረጃዎች ተመርኩዘን የግል ቢጋር አናዘጋጅም ወይም የእርስዎን መረጃዎች ለሌላ የግል ድርጅት አሣልፈን አንሰጥም፡፡ የእርስዎን መረጃ ለንግድ ጉዳይ ለመጠቀም ስንልም አንይዝም፡፡

የላኩልንን ኢሜል ከሌላ የፌደራል መንግሥቱ ተቋም ጋር የምናጋራው እርስዎ የጠየቁን ጉዳይ ከዚያ ተቋም ጋር ግንኙነት ያለው ከሆነ ወይም በሕግ ከተገደድን ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም ኢሜሎችን ጨምሮ ሌሎችም ሠነዶችን እንድናቀርብ በተወካዮች ምክር ቤት ወይም በዳኛ ከተጠየቅን እንሰጣለን፡፡

ለክትትልና ለማጣጣም የሚሰበሰብ መረጃ /ኩኪስ/

“ኩኪ” የሚባለው ኮምፕዩተርዎ አንዳንድ የተለዩ መረጃዎችን ማስታወስ እንዲችል ኢንተርኔት ላይ በነበሩ ጊዜ የከፈቱት ዌብሳይት ኮምፕዩተርዎ ላይ በራሱ የሚጭነው አነስተኛ ፋይል ነው፡፡ ኮምፕዩተርዎ መረጃውን የሚለዋወጠው ኩኪውን ከጣለው ዌብሳይት ጋር ብቻ ነው፡፡ ሌላም ማንም ዌብሳይት መረጃውን አይጠይቅም፡፡ የኩኪዎች ዓይነት ሁለት ነው፤ “የጉብኝት ወቅት” /session/ እና “የማይጠፋ” /persistent/ ይባላሉ፡፡ “የጉብኝት ወቅት” ኩኪዎች በሕይወት የሚኖሩት የከፈቱት ዌብሳይት መፈለጊያ /ብራውዘር/ ክፍት እስከሆነ ብቻ ነው፡፡ መፈለጊያውን ሲዘጉት ኩኪውም ይጠፋል፡፡ “የማይጠፉት” ኩኪዎች ኮምፕዩተርዎ ላይ ለተራዘመ ጊዜ ይቆያሉ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ዌብሳይቶች ለቴክኒክ ጉዳዮች ሲባል የጉብኝት ወቅት ኩኪዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ምክንያቱ በሳይቶቹ ላይ በተሻለና በተቀላጠፈ ሁኔታ መንሸራሸር እንዲችሉ ለማገዝ፣ ወይም ምርጫዎችዎ የሆኑ አካባቢዎችን ከሳይቱ ጋር በቀላሉ እንዲግባቡና እንዲነጋገሩ ለእርስዎ እንዲመቹዎ አድርገው ማረቅ እንዲችሉ ለመርዳት ነው፡፡

አንዳንድ የቪኦኤ ዌብሳይቶች በተለያዩ ጊዜዎች ለሚያደረጓቸው ጉብኝቶችዎ ቅልጥፍና እንዲረዳዎ በማለት የማይጠፉትን ኩኪዎች ኮምፕዩተርዎ ላይ ይጥላሉ፡፡ ለምሣሌ፤ ያረቋቸውን ምርጫዎችዎን በሌላ አጋጣሚ ወይም ጉብኝት ወቅት መጠቀም እንዲችሉ አድርገው ሊያቆይዋቸው ይችላሉ፡፡ በነገራችን ላይ የማይጠፉትን ኩኪዎች ኮምፕዩተርዎ ላይ የሚጥሉ የቪኦኤ ዌብሳይቶች ሁሉ ይህንን እያደረጉ መሆናቸውን በግልፅ ያሳውቃሉ፡፡

በማይጠፉት ኩኪዎችም ይሁን ሌላ ቦታ የተመዘገቡ የግል መረጃዎችዎ እንዲያኛቸው መብት ወይም ፍቃድ ከተሰጠው አካል በስተቀር በምንም ዓይነት ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው አይሰጡም፡፡

የጉብኝት ወቅቱም ይሁን የማይጠፉት ኩኪዎች ኮምፕዩተርዎ ላይ እንዲኖሩ ካልፈለጉ ብራውዘርዎ /መፈለጊያዎ/ ላይ ሊያስቆሟቸው ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ምክንያት አንድንድ የቪኦኤ ዌብሳይቶች አንዳንድ የቅልጥፍና ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡

XS
SM
MD
LG