በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

Ethiopian Refugee Crisis Overview

በሱዳን አል-ቃዳሪፍ ክልል ውስጥ በሚገኘውና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ባለው ኡም-ራኩባ የመጠለያ ሠፈር ውስጥ የምግብ እርዳታ ለመውሰድ የተሰለፉ ከትግራይ ክልል ውጊያ የሸሹ ሰዎች
በሱዳን አል-ቃዳሪፍ ክልል ውስጥ በሚገኘውና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ባለው ኡም-ራኩባ የመጠለያ ሠፈር ውስጥ የምግብ እርዳታ ለመውሰድ የተሰለፉ ከትግራይ ክልል ውጊያ የሸሹ ሰዎች

የኢትዮጵያ የስደት ቀውስ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መሪዎች መካከል የተነሣው ውጊያና እርሱንም የተከተለው ሰብዓዊ ቀውስ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን እንዳያመሳቅል ተሰግቷል።​

የህወሓት መሪዎች ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ፌደራል ወታደራዊ ሠፈሮችን ካጠቁ በኋላ ፌደራል መንግሥቱ “በአጥፊዎቹ የህወሓት መሪዎች ላይ ህግን የማስከበር ዘመቻ” ብሎ የጠራውን፣ የህወሓት መሪዎች ደግሞ “በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተ” የሚሉትን ወታደራዊ ጥቃት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ከፍተዋል። በማዕከላዊ መንግሥቱና በህወሓት መካከል ውጥረት መንገሥ የጀመረው ከወራት ህዝባዊ አመፅ በኋላ አብይ አሀመድ በመጋቢት 2011 ዓ.ም. ወደ ሥልጣኑ ብቅ ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። አብይ ከኤርትራ ጋር የሰላም ስምምነት አደረጉ፤ ንግድን ክፍት ማድረን፣ የፖለቲካ እሥረኞችን መልቀቅን፣ በጎሣ ማንነነት ላይ ተመሥርተው የቆዩ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖችን በአንድ የብልፅግና ፓርቲ ሥር ማሰባሰብን ጨምሮ ሌሎችም የለውጥ እርምጃዎችን ወሰዱ፤ ሥልጣኑንም ለተራዘሙ ዓመታት ገንኖ ከቆየው ከህወሓት እጅ አወጡ። ይሁን እንጂ የተከፈተው የፖለቲካ ሜዳ በሃገሪቱ ውስጥ የጎሣ ቃና ያላቸው ግጭቶችን አቀጣጥሎ ከሰሞኑ የትግራይ ቀውስም በፊት በ2012 ዓ.ም. ውስጥ ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰው መፈናቀሉን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

ትግራይ ውስጥ የተካሄደው ውጊያ በመጀመሪያው ወሩ ውስጥ ብቻ በሺሆች የሚቆጠሩ ህይወቶችን አጥፍቷል፤ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰው አፈናቅሏል ተብሎ ይታሰባል።ቢያንስ ሃምሣ ሺህ ሰው ወደ ጎረቤት ሱዳን ሸሽቶ መግባቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደት ጉዳዮች ተቋም ይናገራል።

የቪኦኤ ጋዜጠኞች ስለ ቀውሱ ለቴሌቪዥን፣ ለራዲዮና ለዲጂታል መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ናቸው። ቪኦኤ ነፃነትና ዴሞክራሲን ለመደገፍ ከሚያከናውናቸው መረጃን የማድረስ፣ የሃሣብ ልውውጦችን የማበረታታትና የማመቻቸት እንዲሁም ሰዎችን የማገናኘት ተግባሩ በተጨማሪ በዓለም ዙሪያ ስላሉ ስደተኞችና ተፈናቃዮች መከራ መዘገብ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው።

XS
SM
MD
LG