ዋሽንግተን ዲሲ —
አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ቢደረግላቸው ጥቅማቸው ለብዙሃን የሚተርፉ የስራ ሀሳቦችን የሚያመነጩ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው።በቴክኖሎጂ ፣ በትምህርት ፣ በንግድ እና በኪነጥበቡ መስክ ብቅ ብቅ ያሉ ወጣት ወጣኒያን ለማሳያነት ይጠቀሳሉ።
ይሁንና መሰል ወጣቶችን በቅጡ የሚያስተባብር ፣ፍላጎታቸውን አዳምጦ ከተገቢው አጋር አካል ጋር የሚያገናኝ፣ የሙያ ድጋፍ እና ትስስር የሚፈጥር ማህበር ባለመኖሩ የወጣቶቹ መልካም ጅምር በአጭሩ ሲቀጭ ይታያል።
መሰል ሁነቶችን ለመቀየር የወጠነ ማህበር ከሰሞኑ ተመስርቷል።"የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር" ይሰኛል። ለምስረታ ወደ ሰባት ወራት የሚጠጋ ጊዜ እንደፈጀ የተነገረለትን ማህበር ዓላማ እና የመጪ ዘመን ዕቅዶች ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ከማህበሩ ፕሬዚደንት ሳሚያ አብዱልቃድር ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።
ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ፦
Your browser doesn’t support HTML5