ሥልጣናችውን እንዲለቁ በገዢው ፓርቲ የተጠየቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዳንት ጆኮብ ዙማ፣ ዛሬ ረቡዕ ባካሄዱት ቃለምልልስ፣ ራሳቸውን መከላከላቸው ተገለፀ።
“ፖላቲካዊ ጫና በማብዛትና ጥፋቴም ሳይነገረኝ ከሥልጣን እንድወርድ የቀረበው ጥያቄ ትክክልና ፍትሐዊም አይደለም” ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሥልጣናችውን እንዲለቁ በገዢው ፓርቲ የተጠየቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዳንት ጆኮብ ዙማ፣ ዛሬ ረቡዕ ባካሄዱት ቃለምልልስ፣ ራሳቸውን መከላከላቸው ተገለፀ።
“ፖላቲካዊ ጫና በማብዛትና ጥፋቴም ሳይነገረኝ ከሥልጣን እንድወርድ የቀረበው ጥያቄ ትክክልና ፍትሐዊም አይደለም” ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ።
ከስድስት ከፍተኛ የገዥው ኤኤንሲ ፓርቲ ባለሥልጣናት ጋር ባለፈው ሳምንት እንደተነጋገሩ የገለፁት ፕሬዚዳንት ዙማ፣ ሥልጣን የመልቀቁ ጥያቄ እንዲዘገይ መስማማታቸውን ጠቅሰዋል።
እናም እስከ መጪው ሰኔ ወር ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ሃሳብ ማቅረባቸውንም ነው አብረው የገለፁት።
ነገር ግን የኤኤንሲ መሪዎች በዚያ ሃሳብ እንዳልተስማሙና፣ በአስቸኳይ ከሥልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸውም ተገልጧል።
ፕሬዚዳንት ዙማ በፓርቲው መሪዎች ጥያቄ መሠረት በቶሎ ከሥልጣን ካልወረዱ፣ ነገ ሐሙስ ፓርላማው (will hold a no confidence vote) የትምምን ድምፅ እንዲሰጥበት ያደርጋል ተብሏል።
የኤኤሲ የገንዘብ ሚኒስትር ፖል ማስሃቲል “ደቡብ አፍሪካ ለዚህ ትዕግሥት የላትም” ሲሉም ለጋዜጠኞች መናገራቸው ተሰምቷል።
የ75 ዓመቱ ዙማ፣ በተለያዩ የሙስናና የቅሌት ውንጀላዎች መካከል፣ ደቡብ አፍሪክን ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት መምራታቸው ይታወቃል።