ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን እስካሁን በእስርዓይ የሚገኙት አራቱ የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች ክሳቸው እንዲነሳና ከእስር እንዲለቀቁ ጉዳያቸውን የሚያየውን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጠየቀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አንድ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት፥ እስካሁን በእስርዓይ የሚገኙት አራቱ የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች ክሳቸው እንዲነሳና ከእስር እንዲለቀቁ ጉዳያቸውን የሚያየውን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጠየቀ።
በመጻፋቸው ብቻ የረጅም ጊዜ እስር ሊጠብቃቸው የሚችሉት አምደኞች ቀድሞውንም ያለበቂ ምክኒያት ነውና የታሰሩት ፍርድ ቤቱ ክሳቸውን ጥሎ በነጻ ሊያሰናብታቸው ይገባል ነው ያለው፤ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን።
በሽብር ተወንጅለው ጉዳያቸው በነገው ዕለት ለሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚታየው አራቱ አምደኞች አጥናፍ ብርሃኔ፥ በፍቃዱ ኃይሉ፥ አቤል ዋበላና ናትናኤል ፈለቀ ናቸው።
Your browser doesn’t support HTML5