የዩትበር አቅራቢዎቹ እስር እና የባለሞያ አስተያየት

Your browser doesn’t support HTML5

የዩትበር አቅራቢዎቹ እስር እና የባለሞያ አስተያየት

ፖሊስ፣ በቅርቡ፥ የፈጠራ ታሪኮችን እውነተኛ በማስመስል ማኅበረሰቡን ሲያሳስቱ ነበር፤ ያላቸውን 11 የዩቱብ ድረ ገጽ አቅራቢዎች ፣ በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

ተጨማሪ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ሒደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የቤተሰብ አማካሪ እና ሞሽን የማማከርና ሥልጠና ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ራቦ፣ “ዩቱበሮቹ ሲያቀርቡት የነበረው ነገር በጣም አስደግጦኛል፤” ይላሉ፡፡

ኹኔታው ሊስተካከል የሚችለውም፣ በአቅራቢዎች ብቻ ሳይኾን፣ ተመልካቾችም ከተሳትፎ እና ድጋፍ ሲታቀቡ ብቻ እንደኾነ ያስገነዝባሉ፡፡