በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሠቆቃ ውስጥ ያለፉ ተማሪዎችን የሥዕል ዐውደ ርእይ የጎበኙ አዳጊዎች፣ የጦርነት ቀዳሚ ተጎጂዎች ሕፃናት እንደሆኑ ጠቅሰው፣ ግጭቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ለአንድ ሳምንት የተጎበኘውና ዛሬ የተጠናቀቀው ዐውደ ርእዩ፣ በጦርነቱ የሥነ ልቡና ጉዳትን ያስተናገዱ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሥራዎች የቀረቡበትና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት ዩ.ኤስ.ኤድ የተዘጋጀ ነው።
ተጎጂዎቹን ተማሪዎች በሥነ ልቡና እና በቁሳቁስ ለመደገፍ፣ ዩኤስኤአይዲ፥ “ሪድ ቱ” የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ሥራ እንደገባ፣ ዲሬክተሩ ዶክተር ጣሰው ዘውዴ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ በዚህም፣ ትምህርት ያቋረጡና ሥነ ልቡናዊ ቀውስ የደረሰባቸው ተማሪዎች፣ ሥነ ሥዕልን በመሳሰሉ ዘዴዎች እንዲሳተፉና ከችግራቸው እንዲያገግሙ ተደርገዋል፤ ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡