የዮሃንስ ህይወት በፀጋ ሲዘከር

አቶ ዮሃንስ ክፍሌ ዳዺ

አቶ ዮሃንስ ክፍሌ ዳዺ ታኅሣስ 16/2013 ዓ.ም. በ81 ዓመት ዕድሜአቸው አረፉ።

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቆርቋሪዎች አንዱ፤ ጋዜጠኛና ኃላፊ፣ ከቀደምት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያዊያን የሥራ ኃላፊዎችና አስተዋዋቂዎች አንዱ፣ እሥረኛ፣ የ “እናት” ተርጓሚ፣ አስተማሪ፣ የቱሪዝም አማካሪ፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የፕሮቶኮል ሹም፣ ግብረ ሰናይ፣ ሥራ ፈጣሪ፣ አቶ ዮሃንስ ክፍሌ አለፉ።

የአቶ ዮሃንስ ህይወት “በክብርና በፀጋ የሚታወስ እንጂ ዛሬ ወደማይቀረው በመሄዳቸው የሚታዘንበት አይደለም” ይላሉ አብረዋቸው የሠሩና በቅርብ የሚያውቋቸው።

“የዮሃንስ ህይወት በፀጋ ሲዘከር” በሚል ርዕስ የተቀናበረውን ዝግጅት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

“የዮሃንስ ህይወት በፀጋ ሲዘከር”