አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ

የቀድሞ የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳለህ

የቀድሞ የየመን ፕሬዚደንት አሊ አብዱላ ሳልህ መገደላቸውን ፓርቲአቸው አረጋገጠ። በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ‘የርሳቸው አስከሬን ነው’ የተባለ ምሥል የያዘ ቪዲዮ እየታየ ነው።

የቀድሞ የየመን ፕሬዚደንት አሊ አብዱላ ሳልህ መገደላቸውን ፓርቲአቸው አረጋገጠ። በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ‘የርሳቸው አስከሬን ነው’ የተባለ ምሥል የያዘ ቪዲዮ እየታየ ነው።

“ሳልህ ለሪፐብሊካቸው ሲከላከሉ ተሰውተዋል” ያሉት የጠቅላላ ህዝባዊ ኮንግሬስ ፓርቲያቸው መሪ ፋዪካ አል ሳዪድ ከዋና ከተማዪቱ ሰንዓ በስተደቡብ ባለ አካባቢ “ሁጢ አማፂያን ሳልህን ገድለዋቸውል” ሲሉ ከስሰዋል።

የሰባ አምስት ዓመቱ አሊ አብዱላ ሳልህ በፖለቲካ ግፊትና በህዝባዊ ዓመፅ [እአአ] በ2012 ዓ.ም. እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ ከሰላሣ ለሚበልጡ ዓመታት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ከዚያም በኋላ ‘በኢራን ይታገዛሉ’ ከሚባሉት ሁጢ አማፂያን ጋር ኅብረት ፈጥረው ሲታገሉ ቆይተዋል።

የቀድሞው ፕሬዚደንት የተገደሉት ኅብረቱ የመፈረካከስ አዝማሚያ እያሳየ በመጣ በሁለት ቀናት ውስጥ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዚደንት ሳልህ ከትናንት በስተያ፣ ቅዳሜ ሁጢዎቹን ታጣቂዎች አውግዘው ከሳዑዲ አረብያ ጋር የመታረቅ ሃሣብ አንፀባርቀው ነበር።

Your browser doesn’t support HTML5

አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ

የሳልህን መገደል ዛሬ ቀደም ብለው ያወጁት ሁጢዎቹ አማፂያን ሳልህ የተገደሉት ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየተጉዋዙ ሳሉ እንደነበር አመልክተዋል። “በኅብረቱ ላይ ሊፈፅሙት የነበረውን ግልበጣ ቀልብሰነዋል፤ ቀድሞውንም ቢሆን በኅብረቱ ላይ ዕምነት አልነበራቸውም” ብለዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ኅብረት የፈጠሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሳልህና ሁጢዎቹ አማፂያን ዋና ከተማይን ሰንዓን ሲያጥለቀልቁ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኣብዱ ራቡ ማንሱር ሃዲ ሃገር ጥለው ለመውጣት ተገድደው በሳዑዲ የሚመራ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል።

አሊ አብዱላ ሳልህ በቅርቡ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር አድርገው “የሀገሪቱ ወደቦች ይከፈቱ፤ በኛም በኩል አዲስ አዎንታዊ ምዕራፍ ለመጀመር ዝግጁ ነን” ብለው ነበር።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አሊ አብደላ ሳልህ ተገደሉ