“18 ሰዓታት ከተጓዝን በኋላ ባህር ውስጥ ገለበጡን”- ከሞት ከተረፉት መካከል

ወደ የመን በመጓዝ ላይ እያሉ ቀይባህር ላይ በአሸጋጋሪዎቻቸው ተገፍትረው ከተጣሉት መካከል የተረፉት ስደተኞች ወደ ባህር የተወረወሩት በአሸጋጋሪዎቻቸው ከተደቀነባቸው መሳሪያ ጭምር ለማምለጥ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

ከእነሱም ውስጥ የተወሰኑት በዋና ሲተርፉ የተወሰኑት ደግሞ ማዕበል እንደተፋቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። አቅም ያልነበራቸው ሕይወታቸው ጠፍቷል ብለዋል። በሌላ በኩል ወደ ባህር ተገፍትረው ከተጣሉት ኢትዮጵያውያን መካከል የሁለቱ አስክሬን ዛሬ ከባህር ላይ መገኘቱን “በባህሩ ዳርቻ ቀብራቸውን በማስፈፀም ላይ ነኝ” ያለ አንድ ኢትዮጵያዊ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል።

የዓለም ዓቀፍ ፍልሰት ጉዳዮች ድርጅት (IOM) በበኩሉ ወደ ባህር ተገፍተረው ከተረፉት አብዛኞቹ መንገድ መቀጠላቸውን አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል አዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

“18 ሰዓታት ከተጓዝን በኋላ ባህር ውስጥ ገለበጡን”- ከሞት ከተረፉት መካከል