በአፍሪካ በምርጫ ወቅት ጋዜጠኞችን ማሰር እና ማዋከብ እንደሚባባስ አስተውለናል - ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በአፍሪካ በምርጫ ወቅት ጋዜጠኞችን ማሰር እና ማዋከብ እንደሚባባስ አስተውለናል - ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች

ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የተሰኘው ለጋዜጠኞች ነጻነት ተሟጋች ቡድን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ዘንድሮ 2024 ዓ.ም ዓመታዊ የሀገሮች የፕሬስ ነጻነት ይዞታ ሰንጠረዡ ከተጠቀመባቸው አምስት ጠቋሚ መስፈርቶች መካከል ከሁሉም በላይ ፈታኙ ሁኔታ የታየው ከፖለቲካ ጋራ የተገናኘው እንደሆነ ያሳያል። ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ማኅበሩ “መንግሥታት የጋዜጠኞን ደሕንነት ሊጠብቁ አልቻሉም” ብሏል።

የአሜሪካ ድምጽ የናይሮቢ ቢሮ ኃላፊዋ ማሪያማ ዲያሎ ጋዜጠኞች በተለያዩ የፖለቲካ ተዋናዮች ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚጠቁመውን የቡድኑን ሰንጠረዥ ተመልክታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።