የትናንቱ ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ቁጥር ከፍተኛው ነው

በዓለም ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ብቻ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበው ሰዎች ቁጥር እስከዛሬ በሃያ ሰዓት ውስጥ ከተገኙት ሁሉ ከፍተኛው መሆኑ ተገለጸ

ሁለት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስድስት አዲስ የቫይረስ መመዝገቡን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል

ካሁን ቀደም የታየው ከፍተኛ ዕለታዊ የአዲስ ተጋላጮች አሃዝ ባለፈው ሳምንት ዕሁድ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሰባ ሰባት እንደነበር ይታወሳል

በበሽታው ምክንያት አሁንም በቀን ቁጥሩ አምስት ሺህ ለህልፈት እየተዳረገ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንትና ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሁለት የቫይረሱ ተጋላጮች የተመዘገቡ ሲሆን አጠቃላዩ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ አልፏል

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንትየነጻነት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በዋይት ሐውስ ባስተናገዱት ዝግጅት ባሰሙት ንግግር በሀገሪቱ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አላነሱም፤ ሃገሪቱ ቫይረሱን መዛመት ለመግታት እየታተረች ቢሆንም ፕሬዚደንቱ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ስትራተጂያችን በጥሩ ሁኔታ እየተራመደ ነው ብለዋል

እስከዓመቱ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ክትባቱን ወይም መድሃኒቱን ማግኘታችን አይቀርም ሲሉም ተናግረዋል

በሳይንቲስቶች ዕምነት ግን በዚሁ ዓመት ውስጥ ከተገኘ በሚያስገርም ሁኒታ ከተፋጠነ ብቻ ነው ባዮች ናቸው