የቢኤ 2 ቫይረስ ዝርያ የኮቪድ ወረርሽኝን ሥጋት ቀስቅሷል

የማጠናከሪያ ክትባት

ቢኤ 2 ተብሎ የሚጠራው የኮቪድ-19 ቫይረስ ዝርያ በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ አገሮችን በተጠንቀቅ እንዲቆሙ እያደረጋቸው መሆኑ ተነገረ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ በተለይ ዕድሜያቸው ከ50 በላይ ለሆኑ ሰዎች የታሰበው ሁለተኛው የማጠናከሪያ ክትባትም የባለሥልጣናትን ይሁንታ ማግኘቱ ተመልክቷል፡፡

ከኦሚክሮን ጋር የተያያዘ ዝርያ ያለው መሆኑ የተነገረለት ቢኤ 2 ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ መታየቱ ይፋ የተደረገው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን ባሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ሥጋት የፈጠረ ዋነኛው የቫይረስ ዝርያ መሆኑ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ቻይናና በሻንጋይ ያገረሸውን ወረርሽኝ እየተዋጋች ሲሆን ቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋባት ነው በተባለው እንግሊዝም ለቫይረሱ በተጋለጡ ሰራተኞች ሳቢያ የአየር በረራዎች መስተጓጎላቸው ተነግሯል፡፡

ሁለተኛውን የማጠናከሪያ ክትባት የወሰዱት የዩናይትድ ስቴት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑት አሜሪካውያንም ክትባቱን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡